Posts

Image
ማስታወሻ፤ ዘሐዲስ አለማየሁ
ታህሳስ ወር 1953 ዓ.ም ኢትዮጵያ ውስጥ ከተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በኋላ መወሰድ ስላለባቸው የፖሊሲ እርምጃዎች በክቡር አቶ ሐዲስ አለማየሁ ለግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ጥር 23 ቀን 1953 ዓ.ም የተፃፈ ማስታወሻ፡-

ማስታወሻ በቅርቡ በኢትዮጵያ ተነሥቶ ያለፈው ሁከት፤ ለኢትዮጵያ ደህንነትና ግርማዊነትዎ ለወጠነው ሥራ መልካም ፍጻሜ የሚመኙትን ሰዎች ሁሉ እጅግ ሊያሳስብና የእውነተኛ ስሜታቸውን ሳይደብቁ በቅንነት እንዲገልጹ ሊያደርጋቸው ይገባል ብዬ ስለማምን እኔም ከነዚህ ሰዎች እንዳንዱ የሚጠቅም የመሰለኝ አሳብ ከዚህ ቀጥዬ ለማቅረብ እንዲፈቀድልኝ በፍጹም ትሕትና እለምናለሁ።
ማናቸውም ነገር መነሻ ምክንያት ሳይኖረው… እንዲሁ ከደልዳላ ሜዳ አይፈልቅም፤ ወይም ከጥሩ ሁከት አይነሣም፤ እንዲህ ለምሳሌ - አለመደሰት፤ ወይም ቅርታ - ከሌለ ሁከት አይነሣም፤ እንዲህ ላለውም አለመደሰት፣ ወይም ቅርታ  ምክንያት የሆኑትን ነገሮች በጊዜ መርምሮ ካላስወገዷቸው፣ ይዋል ይደር እንጂ ሁከት መነሳቱ አይቀርም። አንዳንድ ጊዜ በሕዝብ መሐከል ቅርታ መኖሩን የሚያውቁ ሰዎች ተቆርቋሪዎች ሆነው በመታየት ለግል ዓላማቸው መሣርያ ያደርጉታል። ምናልባትም በቅርቡ በኢትዮጵያ ሁከት ያስነሡት ጥቂት ሰዎች በዚሁ መንፈስ የተመሩ ናቸው ለማለት ይቻል ይሆናል።
የሆነ ሆኖ አለመደሰት፤ ወይም ቅርታ ካለ ሁከት የሚነሣበት ጊዜ፤ የሚነሣበት መልክ፤ የሚያነሡት ሰዎች ወይም ዓላማው የተለያዩ ይሁኑ እንጂ መነሳቱ ስለማይቀር ከሁሉም የሚሻለው መነሻ የሆኑትን ምክንያቶች በጊዜ ደህና አድርጎ መርምሮ ማስወገድ ነው።
ለማናቸውም ነገር መነሻ የሆነው ሥሩ እንደተደበቀ ተቀምጦ ከላይ የሚታየውን ቅርንጫፉን ብቻ ቢጨፈጭፉትና ለጊዜው እንኳ የጠፋ ቢመስ…
Image
Image
የገናው መልእክት

በሰሎሞን ተሰማ ጂ.http://semnaworeq.blogspot.comEmail: solomontessemag@gmail.com

ከሁለት ሺስምንት (2008) ዓመታት ገደማ በፊት፣ በይሁዳ አውራጃ ልዩ ስሙ ቤተልሔም በተባለ ሥፍራ፣ ከድንግል ማርያም አንድ ሕፃን ተወለደ፡፡ ይህም ድርጊት፣ የዓለም የታሪክ አቅጣጫ የተለወጠበት መሆኑን ሰዎች ለሃያ ክፍለ ዘመናት ያህል ተርከውታል፡፡ ፈጣሪ አምላካችን፣ በማይተረጎም ምሥጢር ሰው ሆኖ የተወለደው የዛሬ 2009 ዓመታት ገደማ ነው፡፡፡፡ በሮማውያን አምባገነኖች ትእዛዝም፣ እንደ አደገኛ ወንበዴዎች በመስቀል ላይ ተቸንክሮ እንዲሞት ሆነ፡፡ ከዚያም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤው የሞትን ግዛት ድል እንደነሣና፣ በትምህርቱም ዘላለማዊ ደኅንነትን እንደገለጠ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ስለዚህም፣ በየዓመቱ - በገና ዳቦ፣ በመዝሙርና በዝማሬ፣ በገና ጨዋታ፣ በድግስና በደስታ፣ እንዲሁም በእልልታ - ተከታዮቹ ሁሉ የቤተልሔም በረት ውስጥ የተወለደውን ሕፃን ልጅ ታሪክ ይጫወታሉ፤ ያወጋሉም፡፡ ይኼ መቼም ካመት ዓመት የማይጠገብ ታሪክ (story) ነው፡፡ የልደት በዓል-ያለፈ ታሪክ ትውስታም ብቻ አይደለም፡፡ የወደፊቱንም ዘላለማዊ ተስፋ መግለጫም ጭምር ነው፡፡ “ሰላም በምድር ትሁን፣ በሰዎችም መካከል በጎ ፈቃድ ሁሉ ይሁን!” ሲሉ መላእክትም ከአርያም ዘምረዋልና፣ የገና በዓል ታሪክ ብቻ አይደለም፡፡ ክርስቶስም፤ “እኔ፣ እስከ ዘመናት ፍፃሜ ድረስ ከናንታ ጋር ነኝ፤” ብሏልና በዓሉ ዘላለማዊ ተስፋም ነው፡፡ 
ዛሬ በዓለማችን ላይ ከሦስት ቢሊዮን በላይ ክርስቲያኖች እንደሚገኙ ይገመታል፡፡ ሆኖም፣ የገና በዓል መንፈሥ የክርስቲያኖች ብቻ አይደለም፡፡ በወንድማማችነት፣ በፍቅርና እርስ-በርስ በመዋደድ ላይ የተመሠረው የክርስቶስ ትምህርት ዋና ዓላማ…